ምህረቱ በዛልኝ

103

ምህረቱ በዛልኝ /2/ ጌታ አሰበኝ
ፀጋውም በዛልኝ /2/ ኢየሱስ ጎበኘኝ
ታይቻለሁ ምስጋናን አበዛለሁ
ተሰምቺያለሁ ሌላ ምን እላለሁ /2/

እንባዬን አበሰው ልቤን ሐሴት ሞላው
ከምስጋና በቀር እኔ የለኝም የምለው
እርሱ ስለሆነ ብርሃን እና ደህንነቴ
አልፈራም ከለላ ሆኖልኛል ለህይወቴ
ደስታዬ ወሰን አለፈ እልልታን ላሰማ
እንዲህ ላከበረኝ ላቆመኝ ፀሎቴን ላሰማ

ታይቻለሁ ምስጋናን አበዛለሁ
ተሰምቻያለሁ ሌላ ምን እላለሁ /2/

38 አመት ባልጋ ላይ ተኝቼ
ወደፈዋሽ ውሀው ሚጥለኝ አጥቼ
መታሰሬን እየ ኢየሱስ ደረሰልኝ
አልጋህን ተሸከም ተነስተህ ሂድ አለኝ

በሀጥያት ወድቄ ተጨንቄ ሳላ
ፍርድ እንዲፈርድብኝ ወደኢየሱስ ቀረብኩ
ጥበብ ባለው ቃሉ ሲናገር የኔ አባት
ከሳሾቼ ሽሹ አገኘሁ ምህረት

ባሌ የሞተብኝ ደሃ መበለት
አንድ ያይኔ ማረፊያ ልጄ ቢሞት
የቃሬዛውን ጫፍ ኢየሱስ ሲነካ
ልጄ ከሞት ነቃ ለኔ ሌቱ ነጋ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top