እንደምን ብዬ

106

እንደምን ብዬ እንዴትስ ላውራ
የአንተ መንፈስ በውስጤ ሠራ
ለክብርህ ዛሬ ያዘምረኛል
የሱሴ በኔ ድንቅ ሰርተሃል
አባቴ በኔ ውብ አድርገሃል

1. የጨለመ ሕይወት ባንተ በርቶልኛል
ያለፈው ስቃዬ ዛሬ ከኔ ርቋል
ከንቱ መዋተቴን ከኔ አስወገድክልኝ
ስለዚህ ላንተ ክብር በቤትህ ዘመርኩኝ
አንተን አመለኩኝ

2. ውስጤንም በሀሴት አንተ ስትሞላ
ላዘነችዉ ልቤ ስትሆናት ከለላ
አይዞህ አለሁልህ ብለህ ስትደግፈኝ
በጠባቂነትህ ዛሬ እዚህ ቆምኩኝ
ሀሴት ተሞላሁኝ

3. በአንደበቴ ሁሉ ቃልህን ስታፈስ
በረከት ሊሆነኝ ቃላቴን ስትቀድስ
አቤቱ ድንቅ ነህ ከሁሉም የበላይ
አቻ የለሌህ ነህ በምድርም በሰማይ /2/

4. የእስራት ገመዴን ፈተህ ስታወጣኝ
መባከኔ ቀርቶ በአንተ አሳረፍከኝ
ሰውስጥ እኔነቴ ሰላምህን ስታፈስ
ነፍሴ እርካታ አገኘች የሀሳቤ ሲደርስ
በአንተ ስዳስስ

5. ዝቅተኛ ነኝ ስል አንተ አከበርከኝ
ከአመድ ትቢያ አንስተህ ከፍ /2/ አረከኝ
በፀጋህ አንጽተህ እንደልቤ ሆንኩኝ
ሌላማ ምን ልበል የሱስ ክበርልኝ
ጌታ ክበርልኝ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top