ኦ ማደሪያህ ይገርማል

113

በተጣለውና በተዋረደው
በተናቀውና ቀድሞ በተረሳው
አንተ በሱ አለህ ትከብርበታለህ

ድንቅ ያሰኛል ስራህ ማደሪያህ ይገርማል

ኦ ማደሪያህ ማደሪያህ ይገርማል
ኦ ዙፋንህ ዙፋንህ ይደንቃል
ይገርማል 6

የወደድን ወደህ ክብርን ትሰጣለህ
ለቅዱስ ማደሪያህ ታሰናዳዋለህ
የኔ ጌታ ውዴ ማደሪያህ ይገርማል
የተጣለን አንስተህ በእሱ ታድርበታለህ

ከፍ ያለውን ትተህ ዝቅ ያለውን ወደህ
ያማረውን ንቀህ ለተጣለውን ከብረህ
ንፋግ ነህ ተብሎ በሰዎች እይታ
አንተ ግን አረከው መክበሪያ ማደሪያ

ኦ ማደሪያህ ማደሪያህ ይገርማል
ኦ ዙፋንህ ዙፋንህ ይደንቃል

ይገርማል /6/
ይደንቃል /6/
ደስ ይላል /6/

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top