ዳገቱን ወጣነው በአንተ
ስንቱን ጉድ አለፍነው በአንተ
ብዙ ነው ያአለፍነው በአንተ
እልፍ ነው የአለፍነው በአንተ
አቤት ቸሩ ጌታ
እረ እንዴት እንዴት ድንቅ አባት ነህ
እውነተኛ አዛኝ ለኛ
እዛኛችን ነህ አባታችን /2/
በፍፁም የለም ባልንበት እኛን የሚረዳ
ተገኝቶ ኣባት የሆነን በዚያ ምድረ በዳ
ሰው አይደል አንተ ብቻ ነህ ክብር ለአንተ ብቻ
አየነው ለካ ከአንተ ጋር ኑሮ ይመቻቻል
ማን አፈረ ማን ተገኝቶ አንተ ባለህበት
እናያለን እንሰማለን በአንተ የሰመረለት
ማበሉ ለኛ ፀጥ አለ ምስክር አለኸን
የሚሳንህ የለም ጌታ ረካን በእጅህ ታምነን
ለክብርህ ዜማን እንዘምር ወጥተን ከፍታ ላይ
ለጠላት ሐዘን ይታወጅ ደስታችንም ይታይ
ለነገም ተስፋችን ጌታ ለዚህም ያበቃን
ጉዞአችን ወደአንተ ይምራን አንተው ነህ ያለኸን
