የህይወቴ ማጣፈጫ

118

የህይወቴ ማጣፈጫ ቅመሙ አንተ ነህ
ያውዳል መአዛህ ይሥባል ውበትህ
አንተ ስትኖር ነው እኔነቴ የሚያምረው
መኖር ማለት ነእኔ አንተ ስትኖር ነው
አንተ ስትኖር ነው/2/
ጌታ ስትኖር ነው/2/

የህይወቴ ትርጉም አንተ ነህ ኢየሱሴ
አምራ ተሽቀርቅራ ምትታየው ነፍሴ
ሌላው ሌላውማ እንዴት ያረካታል
ያንተ ልዩ ስፍራ መች ይተካላታል

አለም የእኔ ሆና ሁሉ ቢሞላልኝ
አንተ የሌለህበት ትርጉምም አይሰጠኝ
የሁሉ ጅማሬ ፍፃሜ አንተ ነህ
ከምንም ነገር ጋር የማንወዳድርህ

መራራ ህይወቴ በአንተ እጅግ ጣፈጠ
የጭንቁ ዘመኔ በአንተ ተለወጠ
ተመቻችቻለሁ ባንተ ትከሻ ላይ
ከኣንተ አስበልጬ ሌላ ሌላ እንዳላይ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top