ዕዳ ነበረብኝ ገንዘብ የማይሽረው
ብዙ አልማዝ ዕንቁ ችሎ
የማይሸፍነው
ነገር ግን እየሱሴ ፍቅር ግድ እያለው
ከሰማያት ወርዶ ዕዳዬን ከፈለው
ዕዳዬን ከፈለው /2/ በደሙ አጠበው
በነጋ በጠባ ጠላቴ ሲከበኝ
ሽርጉድ እያለ ሞት ሊያስፈርድብኝ
በጉዳዬ መሃል እየሱስ ገባና
አትሞትም አለኝ ምድር ወረደና
ዕዳዬን ከፈለው /2/ በደሙ አጠበው
ዙሪያዬ ጨልሞ ሞቴን ስጠባበቅ
እኔንም ከአብ ጋር አጥቼ ሚያስታርቅ
ከሰማይ ሰማያት እየሱስ ወረደ
ኃጢያቴን በደሌን ሁሉ አስወገደ
በደሙ አጠበው ዕዳዬን ከፈለው /2/
የእኔ ማንነት ትርጉሙ እንዳይጠፋ
በደሙ አጠበው እርሱ አይቶ አበሳ
የደያብሎስ ዕቅድ ከንቱ ሆኖ ቀረ
የኔ ሕይወት ዛሬ በኢየስስ አማረ
ዕዳዬን ከፈለው /2/ በደሙ አጠበው
