አይቻልም ያለኩት ተቻለ
ታሪኬን በሱ ተቀየረ
አሮጌው ሕይወቴም አማረ
ያ የጭንቁን ዘመን ረሳሁት
ረዳቴን በዓይኔ አየሁት
ስንቱን ጉድ በሱ ነው ያለፍኩት
መከራዬን ይዤ ቀርቤው
አምላኬ እግዚአብሔርን ታምኜው
መች ወደኋላ ሊል አሰኘው
አሳዛኝ ሕይወቴን ቀየረው
በሥጋት የዋጠኝ መዓት
እንዴት አልፈዋለሁ ያልኩት
አለፍኩት በእግዚአብሔር ዕርዳታ
ለርሱ ምን ይሳናል ለጌታ
ይህ የሆነ የሆነው በጌታ ነው/ በእየሱስ ነው
ስለእኔ የማታውቀው ድካሜን ነው
እንዲህ ከወደደኝ ካከበረኝ ካፈቀረኝ
ከእየሱስ ሌላ ወዳጅ የለኝ
በሰው ዓይን ሲታይ ጅምሬ
ትርጉም አልባ ነበር መኖሬ
ዛሬ ግን ያ አልፏል ተረስቷል
በእግዚአብሔር ምስኪኑ ከብሮአል
