ስለ ታላቅነትህ አውጃለሁ
ስለ ቸርነትህ እናገራለሁ
ስለ ቅንነትህ እዘምራለሁ
እግዚአብሔር ሩህሩህና መሀሪ ነው እላለሁ
አምላኬና ንጉሴ ሆይ አከብርሀለሁ
ለዘላለም አንተን ብቻ ከፍ አደርጋለሁ
በየቀኑ በየሰዓቱ ባርክሃለሁ
በዘመኔ ሁሉ ስምህን እቀድሳለሁ /3/
እባርካለሁ /3/
የኔ ጌታ ግርማህ በሰማይ ከፍ ብሏል
በምድርም ሃይልህ ታላቅ ነው ያሽንፋል
ደስ እያለኝ አውጃለሁ ይህን ዝናህ
እርሱ ቅን ነው እርሱ ድንቅ ነው /3/
እያልኩልህ ላዚምልህ
እንደ ሰማሁት በዝና ያንተን /2/
ባሳለፍኩት አጭር እድሜ ያየሁትን
ታላላቅ ስራዎችን እተርካለሁ
በየቀኑ በየሰዓቱ አወራዋለሁ /3/
እናገራለሁ /3/
