ዛሬም ታማኝ

146

ጌታዬ ዛሬም ታማኝ ነው /2/
ለታመኑበት መሸሽጊያ ነው
ለተደገፉት ጽኑ አምባ ነው /2/

ፀሐይን ለኢያሱ ያቆመው
ባህሩን ለሕዝቡ የከፈለው
ከእሳት ልጆቹን ያወጣው
እግዚአብሔር ዛሬም ታማኝ ነው
ጌታ እግዚአብሔር ዛሬም ታማኝ ነው

ሽባውን ከአልጋ ያስነሳዋል
እንደ እንቦሣ ያዘልለዋል

ሞተ ተብሎ ላበቃለት
ሕይወት ይሰጣል ምን አቅቶት
ነፍሱን ይዘራል ኢየሱስ ምንተስኖት

ማዕል በቃሉ ፀጥ ያደርጋል
ሰይጣን በስሙ ይታዘዛል
በዝማሬ ውስጥ በአምልኮቱ
ይበጣጠሳል ሰንሰለቱ
ይንቀጠቀጣል በኃይል እሥር ቤቱ

ከቶ አይረታም የኛ ጌታ
በጦርም ሆነ በሁካታ
ነፍሱን ለኃጢያት የሰጠው
ኢየሱስ ዛሬም ፍቅር ነው
አልተለወጠም ዛሬም ታማኝ ነው

ወዳጅም የለም ከእርሱ ሌላ
ፍቅሩም ሚጣፍጥ ከወለላ
ጠንካራ ድጋፍ ፅኑ ምርኩዝ
ጌታ ብቻ ነው የደሃ ወዝ
ኢየሱስ ብቻ ነው የኃጢያታችን ደሞዝ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top