ከእመቤታችን የነሳውን ስጋ

153

ከእመቤታችን የነሳውን ስጋ
አደረገው ላዳም ልጅ ፍለጋ

ይህንን አድርጉ ላዳነን ከአደጋ
ምስጋና ይሁን ሲመሽም ሲነጋ /2/

አምላክ ወስብአ አንተ ክርስቶስ
ምግብ ሰራህ የሚሆን ለነፍስ
አዘጋጀኸው በእለተ ሐሙስ
እርሱም ሆነ ማህተም የማይፈርስ /2/

የተራበውን ነብዩ ኤልያስን
መገብከው አንተ ህብስትና ወይን
አበረታኸው አርባ ሌት ተቀን
ምሳሌ ሆነ ለሚስጥረ ቁርባን /2/

ነፍሳችን ታገኝ ዘንድ እርካታ
እንዲረዳትም ለዘለቄታ
እንዲጠብቃት ባንተ ላይ ያላት
እምነቷ ሁሌ መግባት የሰራዊት ጌታ

የሚጠቅም ለነፍሳችን ህይወት
ወደርሱ እንቅረብ እንስገድለት
እንድንለምድ እርሱን ደስ ለማሰኘት
እንመገበው በፋሲካ ወራት

መለኮታዊ ህይወት የሚፈውስ
የሚያጠግብ የተራበችን ነፍስ
ምግብ ሚሰጠን ዘውትር ይቀደስ
ከኋሌ ኩሉ ኢየሱስ ክርስቶስ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top