ላረክልን ሁሉ ተመስገን እንላለን
አንተን በመታመን ዛሬ እናቅዳለን
መጪውን እንደፈቃድህ ላንተ እንተዋለን
ዳግም በፊትህ ለምሥጋና አብቃን /2/
ደካሞች ነንና ለመጪው እንበርታ
ንስሐ እንገባለን ቀርበን ወደ ጌታ
ብለን አቅደናል ሁላችንም ዛሬ
አንተን ተማምነናል እስኪ አሳየን ፍሬ
ጌታን ተቀብለን አምነን እንድናለን
ዘወትር ፊቱ ወድቀን እንሰግድለታለን
የሱን ድንቅ ሥራ እንመሰክራለን
ብለን አቅደናል እንደ ፍቃድህ ይሁን
ሸለቆ እንወርዳለን ዳገቱን እንወጣለን
ረጅም መንገድ ሄደን ዘርን እንዘራለን
ከእርሻችን ፍሬ እንሰበስባለን
ብለን አቅደናል እንደፍቃድህ ይሁን /2/
ክረምቱ ሳይመጣ ቤት እንገነባለን
አንድ አካል አንድ አምሳል ሆነን እንኖራለን
ሌላም ሌላም ብለን ብዙ አቅደናል
አንደፍቃድህ ይሁን በአንተ ላይ ጥለናል
