ክቡር ነህ የኛ ጌታ

144

ክቡር ነህ የኛ ጌታ ክቡር የኛ የሱስ
ትልቅ ነህ ጌታ በኃይልህ አንዳች የለም የሚሳነህ
ያንተ ነን ደስ ይለናል
ልጆችህ ነን ያኮራናል
የሚያስፈራን ነገር የለም እንኖራለን ለዘላለም

በጦር ሜዳ ጀግና ጦረኛ
ልጆችህን ትተህ የማትተኛ
ከአውሬ ሁሉ ጠባቂ ነህ
ጥማችንን ሁሉ አርኪ ነህ
ጌታ አንተ አርኪ ነህ

ሰው ሲጨነቅ አይተህ የምትራራ
ምታወጣን ከጭንቅ መከራ
በችግር ጊዜ ፈጥኖ ደራሽ
የሕይወትን ተራራ አፍራሽ
ጌታ አንተ ነህ ፈዋሽ

ዝቅ ያለውን የምታነሣ
መልካሙን ዜና ምታወሳ
ታላቅ ነህ ብለህ ምታፅናና
ክቡር ነህ ብለህ ምታዝናና
ይገባሃል ምሥጋና

ለደከመ እረፍት የምትሠጥ
ለተጠማ የምትሆን መጠጥ
የተራበንም ሆድ የምትሞላ
እኛ አንፈልግም ከአንተ ሌላ
ጌታ ነህ ብለናልና

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top