ልብህን የሞላው ፍቅር ነው የሚስብ ሁሉንም
ቀንበርህ ቀላልና ልዝብ የሚሸከመው ማንም
ሸክማችን ሲከብደን ኑ ወደእኔ የምትል
በልብህ የዋህና ትሁት ጭንቁን የምታቃልል
1. ጎንህን ወጋነው ጥላቻን መርጠን
ቅኑን ማሰብ ትተን ልንጎዳህ ብለን
ቁስልህ ፈዋሽ የሚሆን የሚለወጥ ለበጎ
አየነው ልብህን የሚራራልን ቶሎ /2/
ልብህን የሞላው ፍቅር ነው የሚስብ ሁሉንም
ቀንበርህ ቀላልና ልዝብ የሚሸከመው ማንም
ሸክማችን ሲከብደን ኑ ወደእኔ የምትል
በልብህ የዋህና ትሁት ጭንቁን የምታቃልል
2. የአንተ የዋህነት ሩኅሩህ ነው ለዓለም
ለሚጠሉህም ቢሆን ከቶ ለራቁህም
ዘወትር ምህረት እንጂ አንተ ቂም አታውቅም
ፍቅርህ የሚመራህ የምትሆን ለሁሉም /2/
ልብህን የሞላው ፍቅር ነው የሚስብ ሁሉንም
ቀንበርህ ቀላልና ልዝብ የሚሸከመው ማንም
ሸክማችን ሲከብደን ኑ ወደእኔ የምትል
በልብህ የዋህና ትሁት ጭንቁን የምታቃልል
3. ሰፊ ነው ልብህ ቀርበው ላወቁህ
ከዛ እስከዚህ ብለው ፍፁም የማይለኩት
በእቅፍህ ውስጥ ያሉ ቁጥር የማይገልፃቸው
የአንተ ወዳጅ ናቸው ፍቅርህ የገዛቸው /2/
ልብህን የሞላው ፍቅር ነው
ልብህን የሞላው ቸርነት ነው
ልብህን የሞላው ምህረት ነው
ልብህን የሞላው ትዕግስት ነው
ልብህን የሞላው ፍትህ ነው
ልብህን የሞላው ቅንነት ነው
