1. እስኪ አስተምረን ጌታ መሽካከም
አንዳችን ለአንዳችን እንቻል መተሳሰብ
አቅሙ የበረታ ይቁም ለደካማው
መረዳዳት ይንገስ ይህ ጸሎታችን ነው
አስተምረን ልገሳ አስተምረን ፍቅር
የምድራችን ተስፋዋ ሁን ህልውናዋ /2/
2. አንዱ እየቆዘመ በሀዘን በችግር
ሌላው ተደላድሎ ይኖራል በክብር
ሰው ምንድን ነው ትርፉ እንደዚህ መኖሩ
እንዴት ያዛልቀው እራሱን ማፍቀሩ
3. ፍጹም አዛኝ መስሎ ከንቱ እንባ ማንባት
ምድራችን ሽንገላ እረ ይህ አይረባት
በፍቅር እንበርታ በእውነት እንዋደድ
እግዚአብሔር ባርኮቱን በእጥፍ እንዲያወርድ
