የእግዚአብሔር ልጅ የታል
ብሎ ለመጣ
ሽቶ እጣን ከርቤውን ይዞ ለወጣ
መንገዱ ቀንቷልና ሊያገኝ ንጉሡን
አውቋል መምጣቱን ጌታ መወለዱን
ተወልዷል አማኑኤል በቤተልሔም
በእልልታ ደምቃ ቆመች ኢየሩሳሌም
መጣ ሊያነፃን ጌታ ከኃጢያታችን
አዲስ ምዕራፍ ከፈተ በህይወታችን
ቃልም ለኛ ስጋ ሆኖ
ወረደልን ክብሩን ጥሎ
አሁን ደስታ የደስታ ቀን
በመንግስቱ እንዲያስበን
ቤተልሔም /4/
አንተን ብሎ ወጥቶ አንተን
ብሎ መጥቶ
ጌታ ማንስ ያውቃል በስምህ ተረትቶ
በምህረትህ መንገድ በሀሳብህ ለሄደ
ያቀደው ተሳክቷል ይበል ተወለደ
ይምራ ኮከብ ዓለም ይወቅ
ሊቃውንትም ሣይል ደቂቅ
አመጡለት በበረቱ
እጅ መንሻ ነገሥታቱ
