አደራ አደራ አደራ አደራ
በሃጥያቴ ብዛት መቆም እንዳልፈራ
ከጥፋት ሰውሪኝ ሁኚ ከኔ ጋራ /2/
ምድራዊ ሕይወቴ በአለቀ ግዜ
የዘለአለም ዳኛ ፊት ስቆም ደርሶ ጊዜ
ጠባቂዬ ማርያም እንቺ እረዳቴ
በጌታ ፊት ቆመሽ አማልጅኝ እናቴ
በሕይወት እያለሁ ከአደጋ ጠብቂኝ
በሞትኩኝም ጊዜ አምላክ ፊት አቅርቢኝ
የምሕረት እናት ከፍርድ አስመልጪኝ
አማልጂ ማርያም ከሃጢያት አድኚኝ
አሸናፊ ሆኜ የድል አክሊል እንዳገኝ
ከሃጢያት እንድርቅ በፀጋሽ ደፊኝ
መልካሚቷን ምድር በድል እንድጉበኝ
ለዘለአለም ሕይወት በክብር አድርሽኝ
