ምህረት ይሻለናል

262

እግዚአብሔር አባት የፈጠርከን ጌታ
ለፈጸምነው በደል አርግልን ይቅርታ
ሰላማችን በዝቶ ጸሎታችን ሰምሮ
ምህረትህ ያልምደን የጻድቅ ሰው ኑሮ

ምህረት /2/ ኦ ምህረት
ይሻለናል በህይወት
ምህረት /2/ ኦ ርህራሄ ደግነት
ይሻለናል በህይወት

ሁሉም ሀጢአት ሰርቷል ከመንገድህ ወጥቷል
አንድም ጻድቅ የለም ፍጥረትህ በድሏል
ማረን ሁሉን እርሳው አዝነህ ራርተህ ጌታ
ወደ አንተ መልሰን በአንተ ይቅርታ

በአንድ ልብ በፊትህ እንወድቃለን

ምህረትህ እስኪያነሳን እናነባለን እንማጸናለን
ማንም የሚመካ የለም በጽድቅ
አቤቱ ይበቃናል አንተን መራቁ በቃን መራቁ
ዳግመኛ ሳንወርድ ከቅድስት
አዳማዊው ህይወት ይገደልና እርቃናችን ይጽና

ካንተ ተለይተን ወዴት እንሄዳለን
አንተ የህይወት ቃል መሆንህን አይተን
ንስሃ ገብተናል ለበደልነው ሁሉ
በልጅህ ታረቀን ቀድሰህ አርገን ሙሉ

ካፋችን ለወጡ ከፉ ርካሽ ቃላቶች
በምኞታችን ልክ በእጃችን ስህተቶች
በሙላት ገድፈናል ኃጢአታችን በዝቶ
እንዳመዳይ እንጻን አጥራን እንደ ባዘቶ

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top