ተነስቷል

266

የተናገርውን ያለውን የሰሙ
ማመን አቃታቸው ድል መንሳቱን ሲያዩ
እውነት ነው ተነስቷል መቃብር ፈንቅሎ
ስፍራ አዘጋጃለሁ ባባቴ ዘንድ ብሎ

ተነስቷል/2/ ሞትን አሸንፏል
የሰይጣንን ሀሳብ ምኞቱን አክሽፏል

ቃልኪዳን አክባሪ ያለውን ፈጻሚ
ታምር እየሰራ ህዝቡን አስገራሚ
መቃብር ፈንቅሎ ታየ ታምራት
እኛም ተደስትን ስናይ ድል መንሳቱን

እነ መቅደላዊት ሄዱ ሽቶን ይዘው
ሊያገኙት አልቻሉም መቃብሩ ባዶ ነው
እንደ ተናገረው ሞትን ድል አድርጓል
በሶስተኛውም ቀን ከሞት ተነስቷል

እንዘምር በደስታ በሆታ በእልልታ
ሞትን አሸንፎ ድል ለነሳው ጌታ
ይነገራል ላለም አይቆም እዚህ ብቻ
ትንሣኤው ይታወጅ እስካለም ዳርቻ

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top