ከክፉ ከመጥፎ ከጕልማሳ ፀባይ
አመፃን ከማድረግ በጌታ እግዚአብሔር ላይ
ክርስቲያን ወንድሜ ሆይ እራስህን ጠብቅ
ሰይጣን እንዳያጠፋህ በፍፁም ተጠንቀቅ
ሳይመጣብህና ሳይደርስብሀ ያ የጭንቀት ዘመን
በጉብዝናና በደስታህ ጊዜ አስብ አምላክህን
ስልጣኔ እውቀት በተስፋፋበት
በዚህች አለማችን በአሁን ዘመናት
ክፋ ነገሮችና አጉል ፀባያት
አንቀው ይዘውታል አብዛኛውን ወጣት
ነገር ግን ወንድሜ ሆይ ከዝሙት ከስካር
ትድን ዘንድ ከእነዚህ ኃያሉ እግዚኣብሔር
እጆቹን ዘርግቶ ና ወደኔ ይላል
አባታዊ ጥሪውን ላንተ ያስተላልፋል
