በምህረቱ ባለፀጋ ነው

121

በምህረቱ ባለፀጋ ነው
የኛ እግዚአብሔር ሁሌ ፍቅር ነው
ተንኮል አያውቀው አይሆን እንደሰው
ይቅር ይለናል ሳንሰለቸው

1. ከመንገዱ ወጥቶ ለጠፋው ተስፋው
በአለም ፈተና ድካም ለገባው
ምሮት ያፀናናዋል ሀይሉ እስኪታደስ
በእቅፋ ታቅፎ ይሆነዋል ሞገስ /3/

በምህረቱ ባለፀጋ ነው
የኛ እግዚአብሔር ሁሌ ፍቅር ነው
ተንኮል አያውቀው አይሆን እንደሰው
ይቅር ይለናል ሳንሰለቸው

2. በተሰበረ ልብ በፊቱ ላገኘው
ጌታ ምን ተስኖት ለሱም መልስ አለው
ደርሶ ይታደገዋል ተከሳሽ ህይወቱ
ሁሉን አስረስቶ ያደርገዋል ብርቱ /3/

በምህረቱ ባለፀጋ ነው
የኛ እግዚአብሔር ሁሌ ፍቅር ነው
ተንኮል አያውቀው አይሆን እንደሰው
ይቅር ይለናል ሳንሰለቸው

3. መማር አይሰለቸው ለበዛ ሐጥያቱ
ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው ምህረቱ
ይምጣና ይታደስ ሸክሙ የከበደበት
እግዚአብሔር ዛሬም አላለቀበትም
ምህረት/3/ አላለቀበትም /2/

በምህረቱ ባለፀጋ ነው
የኛ እግዚአብሔር ሁሌ ፍቅር ነው
ተንኮል አያውቀው አይሆን እንደሰው
ይቅር ይለናል ሳንሰለቸው

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top