ተሸከመው ሃጥያቴን/2/
ኢየሱስ መድሐኒቴ
በደል ሳይኖርበት ሆኖ በደለኛ
ታስሮ ተገረፈ እንደወጀለኛ
እንደበግ ጐተቱት ግፍን ተቀበለ
ስለኔ ሐጥያት በመስቀል ላይ ዋለ
ፍፁም ፃድቅ ነበር እርሱማ ለራሱ
ስለኔ ሐጥያት እንዲያው መከሰሱ
ደማ ቆሳሰለ ሆነ የሕማም ሰው
ለኔ ሚገባኝን እርሱ ተሸከመው
መቼ እርሱን ታየው የኔ በደል ሐጥያት
ምህረትና ፍቅር ነበር የእርሱ ጥማት
በኔ ምትክ ሆኖ እኔን ነፃ አወጣኝ
እውነተኛ ፍቅሩን በሞት ገለፀልኝ
