ተባረክ

261

ላምልክህ እንጂ በሁሉም ምክኒያት አሃ /2/
ኧረ እኔ አልችልም ስኬቴን ማስላት
ዘምሬ አልቆምም ኑሮን በማስላት አሃሃ
ዛሬም እልሀለሁ ተባረክ ኧኸ ተባረክ
ጌታዬ ተባረክ ተባረክ
ጠላት ይፈር ይስማ ተባረክ አኸ… ተባረክ
አምላኬ ብሩክ ነህ ተባረክ

ምስጋናን የሚሰዋ ያከብረኛል እንዳልከው
በቅዱስ ቃልህ እንደተናገርከው
ስዘምር ልኑርልህ ብዙ ክብር አለኝ እኮ
ሁኔታን አልጠብቅም ላምልኮ

ተባረክ እግዚአብሔር ተባረክ
ተባረክ በአለም ዝናህ ይተረክ
ተመለክ ንጉሴ ተመለክ

ተመለክ ማምለኬን ከወደድክ
ባለ ግርማ /3/ ባለ ሞገስ
ባለ ሞገስ /2/ ነህ ስምህ ይቀደስ

ሲሞላልኝ ዘምሬ ደስታዬ ጥግ ደርሶ
በራድ ስሜት አይደለም መልሶ
ፍጹም ያልተነካካ ከሁኔታዬ ጋራ
ልዩ ምስጋና ይፍሰስ በስፍራህ

ቀስቃሽ እኮ እሱ አይደለም ባህር ቀድሞ ተከፍሎ
ለምስጋና ሚያስነሳኝ ቀጥሎ
ወጀቡ እያለ ፊቴ ጌታ አንተ ነህ ምክንያቴ
አምልኮዬ አይለካም ስኬቴን

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top