በአዲሱ ዘመን ተሰብስበን ዛሬ
እናከብርሻለን ባማረ ዝማሬ
ተመስገኚ ማርያም ስላሰባሰብሽን
ተወደሽ በዜማ ስለአንድነታችን
በአዲሱ አመት አዲስ ሰው እንድንሆን
አንቺን እንድንመስል መጥፎ ልምድን ትተን
ቁርጥ ፍቃድ አድርገን ተነስተናልና
ማርያም ሆይ አደራ አሰጭን ትህትና
መጋደል እንዲቀር የሰው ደም እንዳይፈስ
ጦረኞች ላይ እንዲወርድ የእ/ር መንፈስ
ሰላም እንዲሰፍን በመለው አለም
አማልጅን ቅድስት ሆይ እስከ ዘለአለም
ሰዎች ቀና እንዲሉ ወደ አምላካቸው
ይቅርታ ይጠይቁ ይረስርስ ልባቸው
የመስቀሉን ፍቅር መርምረው ይረዱ
እርጂን ማርያም ሆይ ሰዎች ይዋደዱ
የልጅሽን ደም ፈሶ ከንቱ አልሆነምና
አሁንም ዘወትርም ይስራ እንደገና
በዚህ አንድነታችን እኛ የምንለምንሽ
ሰላም በአለም ላይ ያውርድልን ልጅሽ
