የምታምሪ ንግስት

195

1. የምታምሪ ንግስት
የገነት መአዛ
ለወደደሽ በውነት
ትሆኛለሽ ቤዛ

በጨለመው አለም
ፋናሽ የሚያበራ
ወዳንቺ ስናዘግም
ጠብቂን አደራ

2. እጅሽን ዘርጊልን
ነፍሳችን ስትወጣ
ቆመሽ ከኛ ወገን
ሁኝልን ጠበቃ

3. ለእናት አገራችን
ሁኛት ባልደረባ
ጥላለች እምነቷን
ቃልኪዳን ስትገባ

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top