አትተወኝም አትረሳኝምና አባቴ
ላትለቃት ቃል ገብተሀል ለህይወቴ
ያላንተማ መች ይሆንላታል ነፍሴ
ያከበርካት አንተ ነህና የሱስ
ደካማ ነኝ ከሌለኸኝ ብርቱ ነኝ ስታየኝ
ለሰኮንድም ብትሆን ያላንተ ጠፊ ነኝ
በምህረትህ ብቻ ነው የበሩት አይኖቼ
ፀንቼም የቆምኩት ይዘኸኝ እግሮቼን
አልርቅም ከመንገድህ ኖራለሁ ቤትህ
በረከት ስላሜ ነህ አምንሀለው
ያንተን ቸርነት አይቻለው
የህይወት መንገዴ ነህ አምንሀለው
ጥበቃህን አይቶ ለተደገፈብህ
ትሸፍነዋለህ ከልለህ በደምህ
ወጥመድ አያገኘው እርምጃው ተቃንቷል
ልቡም አይናወጥ በክንድህ ላይ አርፏል
ሌላ የለም የምለው አንተ የኔ
የሚቆም ለዘላለም ሆኖ ጎኔ
ያንተን ቸርነት አይቻለው
የህይወት መንገዴ ነህ ወድሀለው
ስምህ ይጣፍጠኛል አንደበቴን ሳወራ ስናገረው
ባይኖችህ መታየቴኮ ጌታ ከሰው አእምሮ በላይ ነው
ታይቻለው ተጎብኝቼ ባንተ ረፍቴንም ሁሉ አጊንቼ
ታይቻለው ተጎብኝቼ ባንተ ሀሴትን ሁሉ አጊንቼ
አመሰግንሀለው /4/
