አይደለም ምስጋናህ ተው አይደል ዝማሬህ
አይደልም እውቀትህ አይደለም ስብከትህ
ሰው እስኪ ያውቅ እስኪለይህ ተው አይሁን ጾም ጸሎትህ
ክርስትና ይታይ ሲናገር ህይወትህ
አይደለም ምስጋናህ ተው አይደል ዝማሬህ
አይደልም እውቀት አይደለም ስብከት
አትታበይ በልብህ በአስራት በምጽዋትህ
ክርስቶስን አሳይ ኖረኸው በህይወትህ
ከጽድቅ ህይወት ዜማህ በዝቶ ስትዘምር ባደባባይ በመድረክ ላይ
ለማያምኑ አይከብድም ወይ አይጥልም ወይ ትዝብት ላይ ኑሮህ ሲታይ
ቅርብም ያለው ጎረቤትህ እንዲማረክ ባልንጀራህ/2/
ህይወትህ ይናገር ይጥራ ፍሬው ሆኖ የጎመራ ኦ አንተ አዝመራ
አምባሳደር ሆኖ የአባቱ በህይወቱ እንደታየው ያው ስብከቱ
ማነው ሰብኮን ሚያምር ህይወቱ ሲታይ ኢየሱስን መሳይ
አምባሳደር ሆኖ የመንግስቱ በህይወቱ እንደታየ ያው ስብከቱ
ከነቀፋ ነጻ ማነው ሲታይ ኢየሱስ መሳይ
ከዘፍጥረት እስከ ራእይ ቃሉ በቃል ተሸምዶ ብቻ ተሸምድዶ
ያልተኖረ ክርስትና ማብቂያው የት ነው እንዲህ ሄዶ ሄዶ/2/
ከስማችን በላይ አምሮ ኧረ ይታይ ህይወታችን በኑሯችን
ይሄ አይደል ወይ ከእግዚአብሔር የተሰጠ አደራችን ለምድራችን
አምባሳደር ሆኖ……..
በአንድ በስለው ፍቅር ምህረት ደግሞም በቀል ምቀኝነት ዘረኝነት
ተገምደውም እየበቀሉ በራድና ትኩስ ህይወት ላይሆን ስብከት
እስኪ ሚያዩን ይታነጹ እሱ ያውራና ተግባራችን ከአፋችን
በፍሬያችን እንታወቅ ልኩ ይህ ነው የእምነታችን መለኪያችን
አይደለም ምስጋናህ……..
