ለሰው ልጅ መዳን ምክንያት የሆነች
ማደሪያ ለመሆን የፈቀደች
ማርያም እኮ ናት ውድ እናታችን
አገናኛችን አማላጃችን
አምላክ ወደኛ ሊመጣ ወዶ
በአንቺ ለማደር መረጠሽ ፈቅዶ
የአምላክን ምርጫ በመቀበልሽ
አገናኘሽን እኛን ከልጅሽ
ኤልሳቤጥን ስትጐበኛት
ልጇ ዘለለ መንፈስ ሞላባት
ሰውን ከልጅሽ ምታገናኘ
ድግል ማርያም ለኛም ለምኚ
በሰርጉ ግብዣ ወይን ጠጅ አልቆ
የግብዣ ሐላፊ እጅግ ተጨንቆ
የጭንቅ አማላጅ ልጇ ዘንድ ሔደች
ችግሩን ነግራ ወይን አስገኘች
ልጂ በመስቀል ለኛ ተሰቅሎ
ሊሞት ሲያጣጥር ተንጠልጥሎ
እናቴ ሆይ ብሎ ሲጠራት
የሐዘን ሰይፍ ልቧን በእጅጉ ወጋት
ያለአንዳች ምክንያት የሱስ ጌታችን
አዛኝዋ እናቱን እንዲሁ አልሰጠን
የጸጋ እናት ከልጅሽ ፀጋን
ጠይቂልን ለምኝልን
