ምስጋና ይድረስህ ሐያል አምላካችን
ጠላትን ድል ነስተን ለአንተ መሆናችን
እርምጃችን ሁሉ ፍሬ እንዲኖረው
ጌታ ሆይ ጠብቀን በመንግስትህ እንድንኖር
እናመስግነው በእልልታ በደስታ
ስሙ ይባረክ የዘለአለም ጌታ
እናመስግነው በእልልታ በደስታ
ስሙ ይባረክ ጠላትን የሚረታ
ልባችንን ክፈት ቤትህም አድርገው
ቃልህን ለይተን በእርግጥ እንድናውቀው
በምስጋና ሁሌ ፀንተን እንድንኖር
ያኣንተ ፍቃድ ይሁን በሰማይ ለመኖር
በሕዝቦች ሐጥያት ምክንያት የሞተው
ትልቅ ውለታ ነው ጌታ የከፈልከው
ጌታ አምላካችን እርዳን ልጆችህን
ፀጋህን አድለን ትልቅ በረከትን
