ክብር ምስጋና

62

ክብር ምስጋና ይሁን ለሱ /2/
ለአምላኬ ይሁን ለንጉሱ
ክብር ምስጋና ይሁን ለሱ

የተቸገረውን ሰው የምትረዳ ጌታ
ስንጠራህ ትመጣለህ ሳትቆይ ባንዳፍታ
ፍቅር እንዲኖረን ጌታ ሐይልን ስጠን
መንገድን አሳየን እንከተልሐለን

በእግዘአብሔር ሐይል ውዬ እገባለሁ
አቤቱ አባቴ ድንቅን አወራለሁ
በአንተ ደስ እንዲለኝ ሐሴት አደርጋለሁ
ጌታ ሆይ ለአንተ ምስጋና ሰዋለሁ

አምላኬ ወደአንተ እሮጣለሁ
ለዚህ ህይወቴ ጌታን አከብራለሁ
ከንፈሮቼ አንተን በደስታ ይጠራሉ
በመኝታም ጊዜ አንተን ያስባሉ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top