ይደርሳል ጌታ በጊዜው

20

ይደርሳል ጌታ በጊዜ እንደ ተስፋ ቃሉ
በሰዎች ተስፋ ቢቆረጥ አይሆንም ቢሉ
እኔ ግን እጠብቃለው ይሻላል ብዬ/2
እግዚአብሔር እሱ ብቻ ነው የኔ ተስፋዬ/2

አብርሃም እና ሳራ እንደ ተስፋ ቃሉ
ሰጣቸው ይስሃቅን መቼ ባዶ ቀሩ
እጅግ ደስታ ሆነ በሀዘንም ፈንታ
የሀዘን እንባቸው ታብሶ በጌታ

ግራ ቀኝ አይቼ ተስፋ ባይሰጠኝም
ኣምናለው አምላኬን እሱ ኣይጥለኝም
አማራጭ ፍለጋ ወዴት እሄዳለሁ
ቢዘገይም እንኳን እጠብቀዋለው

አለቀ ተብሎ የተደመደመው
የሞተው አልዓዛር እጅግ የሸተተው
እሱም ሕይወት ዘራ ታምር ጉድ ተባለ
ለኔም ታሪክ ገና እግዚአብሔር አለ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top