ከመላኩ ጋራ
እንጅ እንነሳለን
ከገብርኤል ጋራ
እንሰግድልሻለን
ስምሽን ለማሞገስ
አፋችን አጣው
ዜማሽን ለማድረስ
እውቀት አቃተው
ገና ሳትፀነሽ
እግዜር አይቶሻል
ገና እርቀሽ ሳለሽ
እግዜር አውቆሻል
በላይኛው ሰማይ
አንቺ በለጥሽ
ደግሞም በምድርም ላይ
አንችው አማርሽ
ውጋገኑም ቢታይ
ንጊያውም መጣ
አንቺ ብቅ ብትይ
ተስፋችን መጣ
ነግህ ኮከብ ወጣ
ምድሩ በራልን
ፊትሽ በወጣ
እጅግ ደስ አለን
ከፏፏቴ ውሃ
አንቺ ጥሩ ነ
ከማር ከወለላውም
አንቺ ጣፋጭ ነሽ
የሞትን መንገድ
ሔዋን ከፈተች
የሕይወትን መንገድ
ማርያም ከፈተች
የሰማይ ንግሰት
ለኛ እግዜርን
ትልቅ በረከት
ለምኝልን
ኦ ክርስቶስ እየሱስ
ለጥሩ ደሃህ
አፍስ ቡራኬህ
አንተ በእናትህ
