ድካሜን ከላዬ ጥሎ
በኔ ኑር በእኔ እርፍ ብሎ
እስካሁን በቤቱ አኖረኝ
በድል ላይ እያራመደኝ
ይክበርልኝ ይንገስልኝ
ስሙ እግዚአብሔር ነው ይህን ያረገልኝ
ይክበርልኝ ጌታ ይንገስልኝ
ከማንም በላይ ጌታ ነው ያዘነልኝ
ምስጋና እንዲስ ለወደደኝ /3/
ሲመርጠኝ ዳግም ላይጠላኝ
አምላክ ሆነኝ የሚያስብልኝ
ወዳጅ ሆነኝ የሚያዝንልኝ
ዙሪያዬን ሰልፍ እጅግ በዝቶ
ካቅሜ በላይ ተነስቶ
የጠፋው መስሎ ሲታየኝ
እግዚአብሔር ደርሶ ታደገኝ
በእኔ ላይ እርሱ የማያውቀው
አይሆንም እረኛዬ ነው
ከፉዬን ከሩቅ ያውቀዋል
አምላኬ ምን ይሳነዋል
